Sunday, May 15, 2016

እርሱ ሊልቅ ይገባዋል

እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል። የዮሐንስ ወንጌል3:30

ስለ መጥምቁ ዮሐንስን ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ አለ 'እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።' የማቴዎስ ወንጌል 11:11 እንዲህ ተብሎ የተነገረለት ሰው በዘመኑ የነበሩ ሰዎች አንተ ማን ነህ ለው ሲጠይቁት እርሱ ክርስቶስ እንዳልሆነ ተናግሮ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል አለ። በድርጊቱ በሰዎች ላይ ጥያቄ ያ ነሳው መጥምቁ ዮሐንስ በህይወቱ ዘመን ሁሉ በአገልግሎቱ ውስጥ ሲያሳይ የነበረው ከሱ በኋላ ሰውን ሁሉ ከሃጢያት ሊያነፃ የሚመጣውን ክርስቶስን ነበር። ለዚያውም ብዙዎች ክርስቶስ ይሆንን በለው እስኪጠይቁ ድረስ የሚያስገርም ሰው ሆኖ ሳለ እርሱ ግን ሰውን ሁሉ ወደ ክርስቶስ እንዲያዩ ምልክት ይሰጥ ነበር። 

የሚገርመው ነገር ክርስቶስ ስለሱ ሲናገር ‘በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።’  ማለቱን ስናስተውል በምድር እኔ ልጉላ  ግር ግር የሚፈጥር ድንቅና ተዓምር በማድረግ ትኩረት ለራሱ ለሚስብ ሰው ትልቅ መልክት ነው። እኛስ በተሰጠን ነገር በሕይወታችን በዕለት ተዕለት ኑሮሯችን ውስጥእርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል።’ እያልን ይሆን? ወይንስ በጊዜው ንፋስ እየተገፋን እኔ እኔ እያልን ይሆን? በየትኛውም የሕይወታችን ክፍል ውስጥ በቤተክርስቲያን ይሁን በስራ ቦታ ወይ በቤታችን ተግባራችን እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል።’ ይላል?ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል።

እኔ ግን በሥጋ ደግሞ የምታመንበት አለኝ። ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚታመንበት እንዳለው ቢመስለው፥ እኔ እበልጠዋለሁ። በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤ ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ። ነገር ግን ለእኔ ረብ የነበረውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደ ጉዳት ቈጥሬዋለሁ። አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ። ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:4-11

‘እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል’ የምንልበት ልብ እግአብሔር ይስጠን።

No comments:

Post a Comment