ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። ሰቆቃው ኤርምያስ 3:22-23
በራሴማ ቢሆን በጽድቄ ብመካ
እንኳን ለሰው ልተርፍ ለራሴም አልበቃ፣
የጠላቴ ጩኸት ቢደረደር ክሱ
ግን የጌታ ምህረት ሁሉን መታገሱ፣
ከልጅነት እስከእውቀት እኔን ተሸክሞ
እዚህ አድርሶኛል በፍቅሩ ሸልሞ፣
ያልጠፋነውማ ልክ ነው እርግጥ ነው
ስለከበበን ነው የማያልቅ ርኅራኄው።
ሁሌም
የሚገርመኝ በከርስቶስ ስራ በነፃ መዳኔ ሳያንስ እያንዳንዷን ቀን ደግሞ በምህረቱ ተሸክሞ እንደሚያኖረኝ ሳስብ ነው። ምህረቱ
ርኅራኄው የማያልቅበት ስለመሆኑ ክሌላ ቦታ ማስረጃ ማምጣት አይጠበቅብኝም እኔው እራሴ በቂ ማስረጃ ነኝ።
መዝሙረ ዳዊት 136
1 እግዚአብሔርን
አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
4 እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5 ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6 ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
7 ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
8 ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
9 ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
10 ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
12 በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
18 ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
22 ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
24 ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
25 ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
3 የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
4 እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
5 ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
6 ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
7 ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
8 ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
9 ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
10 ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
11 እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
12 በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
15 ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
16 ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
17 ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
18 ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
19 የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
20 የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
21 ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
22 ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
24 ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
25 ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
በፀጋው
አድኖ እንዲሁም በምህረቱ እና በፀጋው እየደገፈ እያንዳንዷን ቀን ለሚመራን ርኅራኄው ለማያልቀበት አምላክ ምስጋና ይድረሰው።
No comments:
Post a Comment