Sunday, May 15, 2016

መታገል ወይስ መጠጋት?

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። የያዕቆብ መልእክት 4:8

ታግሎ ነገርን ከእግዚአብሔር ለማግኝት መጣር አንዳንዴ ደስ ይላል። ምክንያቱም ሰው የድካሙን ውጤት ማየት ስለሚያረካው ። ነገር ግን ከእግዚአብሔ ለማግኘት ከእርሱም ለመቀበል ከመታገል ይልቅ ወደእርሱ መጠጋትን የሚያክል ነገር የለም ። መጠጋት ስንል ግን ምን ማለት ይሆን? የሆነ ቦታ እግዚአብሔር ቁጭ ብሎ እኛ ወደ እርሱ ለመጠጋት የምንሄድ አይነት ሳይሆን ተረጋግተን ካለብን ሁካታና ግር ግር አርፈን ሃሳባችንን ሰብስበን እርሱን ብቻ የምናስብበት ከእርሱ ብቻ የምንሰማበት ሁኔታን ለራሳችን መፍጠር ነው ።

ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። የማቴዎስ ወንጌል 6:6

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ ያለ የኛ እርሱን መፈለግን ሁልጊዜም የሚጠባበቅ ወደ እርሱ ጆሮዋችንን ባቀናን ጊዜ ድምጹን ሊያሰማን ሁሌም ዝግጁ የሆነ አምላክ ነው ። እኛ እንፈልገው እንጂ እርሱ ሊገኝ ዝግጁ ነው ። 

እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። መዝሙረ ዳዊት 145:18

ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። መዝሙረ ዳዊት 65:2

እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት ፤ ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55:6-7

እግዚአብሔር መፈለግ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ የሚገኝበት ቦታ መገኝት ነው።

እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፤ የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55:1-3

እግዚአብሔር እርሱን የሚፈልግ ልብ ይስጠን ።

No comments:

Post a Comment