"ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ
በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።” የማቴዎስ ወንጌል 18:20
ኦ የመገኘትህ ሚስጥር በምንም የማለውጠው
ስትመጣ የሚሰማኝ መንግስተ ሰማያት ነው።
የአንተ መገኘት ይፈጥራል ደስታ
ለሁሉ መልስ ነው ለነፍስም እርካታ
ማምለጫ ዓለታችን መሸሸጊያ ቦታ፤
አንተ እኮ ከመጣህ ከተገኘህ መሃል
የሁላችን ሚስጥር በቅጽበት ይፈታል።
የመሰብሰባችን ዋነኛ ሚስጥሩ
ያንተ መገኘት ነው ትርጉሙና ግብሩ፤
ከጩኸት ያለፈ ከመሟሟቅ በላይ
የአንተ መገኘት ህይወት ይቀይራል
ከቀን ደስታ አልፎ ለዘመን ይሆናል።
ኦ የመገኘትህ ሚስጥር
ጥርጣሬን አስወግዶ በደስታ የሚያሰክር
ልጅነትን አስረግጦ በጠላት ላይ የሚያስደፍር፤
ኦ የመገኘትህ ሚስጥር
ማንነታችንን አስጥሎ አንተን ብቻ የሚያስከብር
ውበትህን አሳይቶ የሚያስነድፍ ባንተ ፍቀር
ኦ የመገኘትህ ሚስጥር።
ኦ የመገኘትህ ሚስጥር።
“ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፤
በምድር ላይ ሁለት ሆናችሁ ስለ ምንም ነገር በመስማማት ብትጠይቁ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል፤ ሁለት ወይም ሦስት
ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት መካከል በዚያ እገኛለሁና።” የማቴዎስ ወንጌል 18:19-20
መገኘቱን እንድንናፍቅ እግዚአብሔር ይርዳን።
No comments:
Post a Comment