ሥርዐትህን እማር ዘንድ፣ በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ።መዝሙረ ዳዊት 119:71
ወርቅ የተለያዩ የጥራት ደረጃዎች አሉት። እነዚህ ደረጃዎች የሚመደቡት በመጨረሻ ወርቅ የሚመስል ነገር እጅግ ብዙ ከሆነ ድብልቅልቅ ካሉ ቆሻሻዎች ውስጥ ተነጥሮ ከወጣ በኋላ ነው። ከዚህ ወርቅ ከሚመስል ነገር ውስጥ ደግሞ ገና ተጣርተው የሚወጡ አላስፈላጊ ነገሮች አሉ። ይህ የወርቅ ደረጃ የሚመደብበት ሂደት ደግሞ ይህን ይመስላል። በአንድ ስሜልተር(smelter) በሚባል እቃ ውስጥ ይህ ወርቅ መሳይ ነገር ከተለያዮ የኬሚካል ውሁዶች ጋር አብሮ ይገባና በ 1600 ዲግሪ ሴልሸስ ደረጃ ሙቅት ይቀልጣል ወይም ይቀቀላል። የዚህም ሂደት ውጤት 80% ብቻ የሆነን ንፁህ ወርቅ ይሰጠናል፣ ይህ ማለት አሁንም ይህ በ80% ንፁህ ወርቅ የመጨረሻው ደረጃ ማለትም
99.9% ነፁህ የወርቅ ደረጃ እስኪደርስ ሌላ የማ ጣራት ሂደትን ያልፋል። አንድን ነገር ብቻ ልብ እንበል፣ በራሳን
ስንፍናና ጥፋት ውጣ ወረድ ውስጥ ልንገባ እንደምንችል። ከዛ ውጭ ግን መንገዳችንን በእግዚአብሔር ፊት መልካም አድርገን እየተጓዝን
ባለበንት ወቅት፣ የህይወታችንም የመጀመርያው ግብ እርሱን ማስደሰት ሆኖ እያለ 'ፈተናው እኮ ለምን?' ብለን የምንጠይቅበት ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን ካገኘነው፤ መልሱ
ከወርቅ የበለጠውን ማንነት የማግኛው መንገድ፣ የማናውቀውን ማንነታችንን የምናውቅበት፣ ከፍ ወዳለው ከፍታ የምንወጣበት፣ የሚጎረብጠው
እና ወደኋላ የሚጎትተው ልማዳችን የሚቀፈፍበት፣ ከሁሉም በላይ የልጁን መልክ የምንመስልበት መንገድ ላይ ነን። ሂደቱ ያማል ውጤቱ
ግን ያደምቃል። በሂደቱ ውስጥ ያለው እያንዳንዱን መንገድ ከቻልን በደስታ ካልሆነም በፀጥታ አልፈን ከአንድ ክብር ወደ ሌላው እንድንሄድ
ይሁንልን። መቼም የጥራቱ ሂደት እስክንሞት ይቀጥላል በየደረጃውም ሂደቱ ይቀየራል። በዚህ በመጥራት ሂደት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ተገብቶ
የማይማሩትን፣ በሽያጭ አንደኛ ደረጃ የያዙትን መጽሃፍቶች አንብበንም ይሁን ከዕውቅ አስተማሪ ስር ለዘመናት ተቀምጠን ብንማርም የማናገኘውን
ትምህርት እንማራለን። ከሁሉ በላይ በፈተናው ውስጥ ስናልፍ ከወርቅ በላይ የሆነው እምነታችን ይሰራል፣ እርሱም በየትኛውም ሁኔት
ውስጥ አይናችን አንድ ቦታ ብቻ እንዲያይ ይሆናል፤ የእምነትችን ጀማሪውና ፈፃሚው የሆንው ክርስቶስ ላይ።ፈተናው እኮ ለምን ካልንማ፣
ፈተናው እርሱን እና እርሱን ብቻ ካውቅነው በላይ እንድናውቀው።
ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ ምክንያቱም
የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ። ምንም የማይጐድላችሁ ፍጹማንና ምሉኣን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን
ይፈጽም።የያዕቆብ መለክት 1:2-4
በፈተና ውስጥ ስናልፍ እግዚአብሔር አይናችንን እርሱ ላይ ብቻ እንድናደርግ ይርዳን።
No comments:
Post a Comment