“. . . በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?” ኢያሱ 1:9
ፍርሃት የሰውን ልጅ በከፍተኛ ሁኔት ከሚቆጣጠሩ ነገሮች ውስጥ የመጀመርያ ደረጃን ሊይዝ የሚችል
ችግር ነው። ይህም ከመሆኑ የተነሳ ይመስላል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 'አትፍራ' የሚለው ቃል እጅግ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰው።
እንዳውም ይበልጥ ለማረጋገጥ 'አትፍራ' የሚለው ቃል በትክክል ምን ያህል ጊዜ ተጠቅሷል ብለን እንጠይቅ። በእርግጥ 'አትፍራ'
የሚለው ቃል 365 ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል። ይህም ቁጥር በአመት ካሉት ቀኖች ጋር እኩል ስለሆነ በያንዳንዱ ቀን
እግዚአብሔር አንዴ 'አትፍራ' ይለናል። ፍርሃት ከእምነት ጋር በተቃርኖ የሚሄድ ጉዳይ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካችውን
ከምናውቃቸው ከሙሴ ጀምሮ በፍርሃት ያልተፈተነ አናገኝም። ከሰው ልጅ የወደፊቱን የማወቅ የተፈጥሮ ጥብቅ ፍላጎት የተነሳ
እርግጠኛ ያልሆንበትን ነገር መጀመር ይከብደናል። እግዚአብሔር ደግሞ 'አትፍራ' ሲለን እያለን ያለው 'በእኔ ተማመን' ነው።
ለዚህም ነው 'ደግሞም ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሁሉ እግዚአብሔር መኖሩንና ከልብ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጥ ማመን አለበት።'
ተብሎ ዕብራዊያን 11:6 ላይ የተጻፈው። እምነታችን እግዚአብሔርን ካስደሰተው ፍርሃታችን ደግሞ ያሳዝነዋል ማለት ነው። ጃክ
ካንፊልድ የሚባል ሰው 'እያንዳንዱ የምትፈልገው ነገር ከፍርሃትህ ድንበር አልፎ ይገኛል' ብሎ ፍርሃት እንዴት አድርጎ ማድረግ
ከምንፈልገው ነገር ውይም ከተጠራንበት ጉዞ ሊያስቀረን እንደሚችል ገልጾታል። የማንፈራው በአንድ ምክንያት ብቻ ነው፣ እግዚአብሔር እኛ ጋር ስላለ።
“ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ እምነቴን በአንተ
ላይ
አደርጋለሁ።
ቃሉን
በማመሰግነው
አምላክ፣
በእግዚአብሔር
ታምኛለሁ፤
አልፈራም፤
ሥጋ
ለባሽ
ምን
ሊያደርገኝ
ይችላል?”
መዝሙረ
ዳዊት
56:3-4
ስንፈራ እምነታችንን በእርሱ ላይ እንድንጥል እግዚአብሔር ይርዳን።
So true... !!!
ReplyDelete