Friday, May 13, 2016

የማይቀያየር ምስጋና

ትንቢተ ዕንባቆም 3:17-19
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል። 

ዮሴፍን ወንድሞቹ ገፍተው ገፍተው ቤተ መንግስት አስገቡት ዳዊትን ሳኦል አሳዶ አሳዶ ምርጥ ንጉስ ካረገው በኋላ ቤተ መንግስት አስገባው አንተስ/አንቺስ እየተገፋሽ ነው? ጠላታችን ገፍቼ ልጥላቸው ነው እያለ ሲደሰት ያልገባው ነገር እግዚአብሔር ወዳየልን እያንደረደረን እንደሆነ ነው ዛሬ እየተንገዳገደን ያለን ብንመስልም ነገ አንድ እርምጃ አምላካችን ወዳየልን እንደተጠጋን ይገባናል ስለዚህ ሁኔታዎችን ሲለዋውጡ በውስጣችን ግን ከሁኔታ ጋር ሊለዋወጥ የማየገባው ምስጋና ነው ይልቁን ሁኔታዎች ግራ ባጋቡን ጊዜ የምናቀርበው ምስጋና ጠላታችንን ግራ ሲያጋባው አባታችንን ደግሞ ደስ ያሰኘዋል   ለዚህም ጳውሎስና ሲላስ በወህኒ ቤት ሆነው ያደረጉተን ማስታወስ ግድ ይላል። የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 16። ዳዊት ሃሌ ሉያ ብሎ በሚጀምረበት ምዕራፍ ላይ ስለ ጠላቶቹ ግፊያ እንዲህ ይላል

አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤ መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው፤ ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንዲነድድ ነደዱ፥ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍኋቸው። ገፋኸኝ፥ ለመውደቅም ተንገዳገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ። ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ። መዝሙረ ዳዊት118:10-14

የአሸናፊነታችን ወይም አሸናፊነታችንን ለማፍጠን ትልቁ ሚስጥር ያለው በልባችን ውስጥ እንጂ በአካባቢያችን ባሉ ሁኔታዎች አይደለም ልባችን ውስጥ ያለው በሁኔታዎች የማይቀያየር ምስጋና ከሆነ አሸንፈናል ማለት ነው።

ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:7-10

ልባችን ውስጥ ያለው ሁሌም በሁኔታዎች የማይቀያየር ምስጋና እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን።

No comments:

Post a Comment