1 ቆሮንቶስ
1፡18 — 31
18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
19 የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና።
20 ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
21 በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።
22 መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥
23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
24 ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
25 ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
26 ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።
27 ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
28 እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
29 ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።
30 -
31 ነገር ግን። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
በመጀመርያ ጥበብን በሁለት ከፍለን እንድናይ ግድ ይለናል፣ የዓለም ጥበብና የእግዚአብሔር
ጥበብ።
በአጭሩ ስንገልገልጻቸው፡
·
የዓለም ጥበብ ጊዜያዊ ነው
·
የእግዚአብሔር ጥበብ ዘላለማዊ ነው
ብዙ ጊዜ ጥበብ ሲነሳ በመጀመርያ የሚታወሰን ጠቢቡ ሰለሞን ነው ብዬ እገምታለሁ።
ታሪኩም በ1 ነገስት 3 እና 4 ላይ ይገኛል።
የሰለሞን ጥበብ በዋናነት ምድራዊ የነበረና የዓለምን ታላላቅ መንግስታት ቀልብ የሳበ
ነበር። የጥበቡም ታላቅነት የሚወዳደረው በዘመኑ ከነበሩ የምስራቅ ሰዎችና ከግብጽ ጋር ነበር። ከነሱም ተወዳድሮ ወደር አልተገኘለትን
ነበር። ነገር ግን የሰለሞንን ታሪክ ስናጠናው በእድሜው መገባደጃ ላይ ልቡ ከእግዚአብሄር እንደራቀና እግዚአብሄር እንዳዘነበት በመጨረሻም
እንደሞተ እናያለን።
ዛሬ ግን የማተኩረው ከሰለሞን የሚበልጠው በሚል ሉቃስ 11፡31 በተገለጸው ላይ ነው።
የሰለሞን ጥበብ ሲያልፍና ሲረሳ የእርሱ ግን ዘላለማዊ የሆነና ተወዳዳሪ የሌለው ነው።
እስቲ ወደ ዋናው መልእክቴ ከመግባቴ በፊት
ጥበብ ምንድን ነው? ወዴትስ ይገኛል? የሚለውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባጭሩ እንይ
ጥበብ ምንድን
ነው?
ምሳሌ 4፡7 ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ያለህን ሁሉ ወይም ያገኘኸውን
ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።
“ሰዎች ሆይ፤ የምጠራውኮ እናንተን ነው፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ።
እናንተ ብስለት የጐደላችሁ፤ ጠንቃቃነትን ገንዘብ አድርጉ፤እናንተ ተላሎች፤ ማስተዋልን
አትርፉ። የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ።
ጥበብ ወዴትስ ይገኛል?
ምሳሌ 15፡33 እግዚአብሔርን መፍራት
ጥበብን መማር ነው፤ወይም ጥበብ እግዚአብሔርን መፍራት ታስተምራለች።ትሕትናም ክብርን ትቀድማለች።
ምሳሌ 19:23 እግዚአብሔርን መፍራት
ወደ ሕይወት ይመራል፤እንዲህ ያለውም ሰው እፎይ ብሎ ያርፋል፤ መከራም አያገኘውም።
ምሳሌ 23:17 – 18 ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ነገር ግን
ዘወትር እግዚአብሔርን ለመፍራት ትጋ።
ለነገ ርግጠኛ አለኝታ
ይኖርሃል፤ ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
ምሳሌ 28:14 እግዚአብሔርን ዘወትር
የሚፈራ ሰው ቡሩክ ነው፤ ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል።
የእግዚአብሔር ፈቃድ
ዳዊት
መዝሙር 40፡8 አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።
መዝሙር 143፡10 አንት አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ
አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
ሓዋ 13:36 “ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን
ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቶአል፤ …”
ጳውሎስ
1 ቆሮንቶስ
1፡1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስ፣
ሓዋ
21፡14 ምክራችንን አልቀበል ስላለን፣ “እንግዲህ የጌታ ፈቃድ ይሁን” ብለን ተውነው።
ሮሜ 8፡5 እንደ ሥጋ የሚኖሩ ልባቸውን በሥጋ ፍላጎት ላይ ያሳርፋሉ፤ እንደ መንፈስ የሚኖሩ ግን ልባቸውን በመንፈስ ፍላጎት ላይ
ያደርጋሉ።
ሮሜ
12፡2 መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ
ታውቁ ዘንድ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ክርስቶስ
ማቴዎስ 6፡10 መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን።
ኢሳያስ 53፡10 መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ
ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም
እንኳ፣ ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
ሉቃስ22፡42 እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፤ ፈቃድህ ከሆነ፣ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ
ፈቃድ ይፈጸም።”
ዪሓንስ4፡34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውን መፈጸም ነው፤
ዪሓንስ6፡38 ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን፣ የላከኝን የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፤
ማቴዎስ 12፡49-50 በእጁም ወደ ደቀ መዛሙርቱ እያመለከተ እንዲህ አለ፤ “እናቴና
ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው፤ በሰማይ
ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና እናቴም
ነው።”
ጥበበ እና
የእግዚአብሔር ፈቃድ
ምሳሌ 19:21 በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።
ምሳሌ 21:30 እግዚአብሔርን ለመቋቋም
የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።
መክብብ2:25 ከእርሱ ዘንድ ካልሆነ
ማን መብላትና መደሰት ይችላል?
(ያለ እርሱ ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመሰ ማነው?)
ማቴዎስ 7፡21 “በሰማይ ያለውን ያባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም።
No comments:
Post a Comment